መዝገብ

Category: የእለት ዜና

ወጪ በሚደረግ ጥሬ ገንዘብ ላይ ከዛሬ ጀምሮ ገደብ ተጣለ

የብሔራዊ ባንክ ገዚ ይናገር ደሴ ዛሬ ግንቦት 11 2012 በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሁሉም የንግድ ባንኮች በቀን የሚወጣው የጥሬ ገንዘብ መጠን ለግለሰብ 200ሺህ፣ ለኩባንያ ደግሞ 300ሺህ እንዲሆን መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ግለሰብ አንድ ሚሊየን፣ ለኩባንያ 2 ነጥብ…

ግብፅ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ላቀረበችው ስሞታ ኢትዮጵያ የ22 ገፅ ደብዳቤ ምላሽ ሰጠች

ደብዳቤውም ቀደም ብሎ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀጣዩ ክረምት የያዘችውን የውሀ መሙላት እቅድ በመቃወም ግብፅ ለፀጥታው ምክርቤት ላቀረበችው የ17 ገጽ የተቃውሞ ደብዳቤ ምላሽ ነው፡፡. በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በተፈረመና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት (UNSC) በቀረበው ደብዳቤ…

ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 3271 የላብራቶሪ ምርመራ 14 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡ ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 11 ወንድ እና 3 ሴት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ9 እስከ 68 ዓመት ባለው…

“የሰው ልጆች አዳዲስ ጥበቦችን እንዲፈጥሩና ያሉትንም እንዲያሻሽሉ ከገፏቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው በየዘመናቱ የሚከሰቱና የህልውና አደጋ የሚደቅኑ ወረርሽኞች ናቸው” ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

“የሰው ልጆች አዳዲስ ጥበቦችን እንዲፈጥሩና ያሉትንም እንዲያሻሽሉ ከገፏቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው በየዘመናቱ የሚከሰቱና የህልውና አደጋ የሚደቅኑ ወረርሽኞች ናቸው” ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን እና ከወረርሽኙ ጋር አብረው ሊከናወኑ ስለሚችሉ የፈጠራ…

በኢትዮጵያ በ24 ሰአት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 35 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 1775 የላብራቶሪ ምርመራ እስካሁን ድረስ ከተመዘገበው ቁጥር ከፍተኛ የተባለውን በ35 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡ ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 17ቱ ወንዶችና 18ቱ ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም…

ባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞች 84 በመቶ መፅደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

በባለፈው ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተተከሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መፅደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፌስ ቡክ ገፅ ባሰፈሩት ፅሁፍ እንደገለፁት በአረንጓዴ ዐሻራ የችግን ተከላ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተከሉት ችግኞች…

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የ2012 የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የ2012 የ 9 ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በውይይቱ ወቅት ኤጀንሲው በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን ማድረጉ፣ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡና…

የተባበሩት መንግሥታት 10 ሺህ ስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን አስታወቀ

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ወደ 10ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው መመለሱን ገለፀ፡፡ ከእነዚህም 10ሺህ የሚጠጉ ሰነድ አልባ ስደተኞች ውስጥ አብዛኛቹ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደሆኑም ተገልጿል ። ከስደተኞቹ መካከል መጋቢት ወር ላይ ሞዛምቢክ ውስጥ ከሞት የተረፉት…

የድንበር ተሻገሪ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በቃሊቲ ጉሙሩክ ጣቢያ ተጀመረ

የድንበር አቋራጭ ከባድ የመኪና አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ለወረርሽኙ ካላቸው ተጋላጭነት አንጻር በወደቡ ገቢ ጭነት ሲያራግፉም ሆነ ወጪ ጭነት ሲጭኑ በሚኖረው ሂደት የዘመቻ ስራው በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሚገኝ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ፡፡ ከአሁን በፊትም በወደቡ የሰው ንክኪ በሚበዛባቸው አካባቢዎችና ገቢ ጭነት…

ባለፉት 24 ሰአት ውስጥ 15 ሰዎች የካሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገው 3707 የላብራቶሪ ምርመራ 15  ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ሚኒስተሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ እንደተገኛባቸው የተረጋገጠው 15ቱም ሰዎች ወንድ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ17 እስከ 38 መሆኑ ታውቋል፡፡ እነዚህም ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው…

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሀገራዊ የሎጀስትክስ ሥራ እንዳይስተጓጎል በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ ተደረስ

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ ከጅቡቲ መንግስት ጋር በቪዲዮ (virtual meeting) ባደረጉት ዉይይት የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል የሎጀስትክስ ሥርዓቱም ሳይተጓጎል በሚሄድበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል፡፡ በዚህ በዉይይታቸዉም የሀገራችንን የገቢና የወጪ ንግድ በዋናነት ከጅቡቲ ወደብ የሚከናወን በመሆኑ አስፈላጊዉን…

የጋራ እሴቶችን በመጠቀም ጠንካራ አገራዊ የሐይማኖት ህብረት ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል

የጋራ እሴቶችን በመጠቀም ጠንካራ አገራዊ የሐይማኖት ህብረት በኢትዮጵያ የመፍጠርን ሀሳብ ያነገበ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በመካሄድ ላይ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተመራው በዚህ ውይይት ላይም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና…

በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ስራ ያጡ ሰዎች ቁጥር 36.5 ሚሊዮን መድረሱ ተገለፀ

በአሜሪካ በባለፈው ሳምንት ብቻ 2.98 ሚሊዮን ሰዎች ስራ ማጣታቸውን ተከትሎ፣ ወረርሽኙ ከተነሳበት እለት ጀምሮ ስራ ያጡ ሰዎች ቁጥርን ወደ 36.5 ሚሊዮን አድርሶታል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ እየተጠቃች ባለችው አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንዲሁም የሟች ቁጥር ከአለም ቀዳሚ ያደረጋት ሲሆን…

ኮቪድ 19ን ለመከላከል ኢጋድ 25 ሺህ ዶላር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ኮቪድ 19ን ለመከላከል 25 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ። ድጋፉ ለሕክምና የሚውሉ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች፣ ጓንቶችና የንጽሕና መጠበቂያዎች (ሳኒታይዘሮች)ን ያካተተ ሲሆን በኢትዮጵያ የኢጋድ የኮቪድ 19 ተወካይ ዶክተር ግሩም ኃይሌ ለጤና…

በአጭር ጊዜ ለህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አስታወቀ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበውን የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ ወይዘሮ መእዛ አሸናፊ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ማከናወን አለመቻሉን ማስታወቁን ተከትሎ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…

ኮሮናቫይረስን ከአለማችን ፈጽሞ ማጥፋት ላይቻል ይችላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ

የዓለም ጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ማይክ ሪያን ቫይረሱ ከአለማችን መቼ ጨርሶ ሊወገድ ይችላል የሚለውን መተንበይ እጅግ ከባድ እንደሆነ ተናገሩ፡፡ ዶክተር ሪያን ጄኔቫ ላይ በተደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት “ይህ ቫይረስ ፈጽሞ ላይጠፋና ከሰው ልጅ ጋር አሁን…

መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ

መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽፈት ቤት አስታውቋል፡፡ በሰአት እስከ 30 ሺህ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግደው ተርሚናል ከቀላል ባቡር አገልግሎትና ከፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ጋር የተሳሰረ እንደሚሆን ተገልጿል። የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና…

ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 2 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የ2650 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ተጨማሪ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገለፀ፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በምርመራ የተረጋገጠው ሁለቱ ሰዎች ወንድ ኢትዮጵያዊያን፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና እድሜያቸውም 24 እና 33 ሲሆን…

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር በዕድሜ ዝርዝር ተከፋፍለው ተገለፁ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መገኘቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ እስከአሁን በላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር በዕድሜ ዘርዝሮ ከፋፍሎ አስቀምጧል። በዚህም መሰረት ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆነ 1 ሰው፣ ከ5 ዓመትና ከዚያ በላይ 7 ሰዎች፣ ከ15 አስከ…

የኮሮናቫይረስን ለማከም ይረዳል የተባለው የሙከራ መድኃኒት በስፋት ሊመረት መሆኑ ተገለፀ

የኮሮናቫይረስን ለማከም ይረዳል የተባለውን የሙከራ መድኃኒት በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አገራት ለማዳረስ በሚያስችል መጠን እንዲመረት ከተለያዩ መድኃኒት አምራች ተቋማት ጋር ስምምነት ተደርሷል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ መዳኒቱ በስፋት እንዲመረት በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ የመድሀኒት አምራቾች ጋር ስምምነት የተፈራረመው ሬምዴሲቬር የተባለውና ለኢቦላ በሽታ ህክምና…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ከደቡብ ክልል የዞን አመራሮች ጋር ውይይት አደረጉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የዞን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ውይይቱን አስመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በብዙ የተፈጥሮ እና የባህል መስህቦች የታደለ…

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በኮቪድ19 ምክንያት የከፋ ችግር ቢመጣ ለመቋቋም የሚያስችል ዝግጅት መኖሩን አስታወቀ

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ግብረ ኃይል በማዋቀር በጥብቅ ክትትል እየተሰራ እንደሚገኝና የከፋ ችግር ቢመጣም ለመቋቋም የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውን በድሬዳዋ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ለምለም በዛብህ አስታውቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንድ ዩኒቨርሲቲ እና አምስት ትምህርት ቤቶች ለማቆያ እንዲሁም አንድ ማከሚያ…

ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 11 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 2424 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ። ይህም እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 261 አድርሶታል። በዛሬው እለት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ19-47 ዓመት…

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአንዲት ጥበቃ ህይወት አለፈ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቴድሮስ አደባባይ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሰራተኛ የነበረች ሴት ከወንድ ባልደረባዋ በተተኮሰባት ጥይት ህይወቷ ማለፉ ተገለፀ፡፡ አዲስ ማለዳ አደጋው ተከሰተ በተባለበት ስፍራ ተገኝታ ለማረጋገጥ እንደቻለችው የጠበቃ ሰራተኛዋ ህይወት ሊያልፍ የቻለው ከባልደረባዋ በተተኮሰ ጥይት ጀርባዋ ላይ በመመታቷ ሲሆን ህይወቷን ለማትረፍ…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማያከብሩት ላይ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተከለከሉ ድርጊቶች የማይቆጠቡት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሽመልስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሀይል ስራው ያለበትን ደረጃ በገመገመበት ወቅት ባደረጉት ንግግር “የኮሮናቫይረስ /ኮቪድ-19/ ስርጭቱ እየሰፋ መምጣቱ ልዩ ትኩረት የሚሻው…

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶችን የሚመረምር እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የሚያጣራ አዲስ መተግበሪያ ይፋ ሊሆን ነው

ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የኖቭል ኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው የሚመረምር እና ብሉቱዝን በመጠቀም ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የሚያጣራ መተግበሪያ በያዝነው የፈረንጆቹ ወር ይፋ ለማድረግ ማቀዱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ ይህ መተግበሪያ ሰዎች ስለሚታይባቸው ምልክት በመጠየቅ የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው ወይም…

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ዛሬ ገምግሟል ፡፡

በባለስልጣን መስራቤቱ የሶስተኛው የሩብ አመት የእቅድ አፈጻጻም ሪፖርት የቪዲዮ ኮንፈረንሱ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ዳይሬክተሮች አማካሪዎችና የቡድን መሪዎች ታድመዋል። በሪፖርቱም ባሳለፍነው 9 ወራት በዋና መንገዶች ማጠናከርና ደረጃ ማሻሻል 77 ኪ .ሜ መንገድ እና በአገናኝ መንገዶች ደረጃ ማሻሻልና ግንባታ እንዲሁም በመንገዶች…

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዛሬ ከኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር የጋራ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

በኢትዮ-ጅብቲ ኮሪደር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና ለመቀነስና ሎጂስትክሱን ለማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ከኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር የጋራ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ሚኒስትሯ የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚባና በሎጅስቲክስ ዘርፉ የሚገኙ ተዋንያኖች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል አገልግሎት…

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው የ1764 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ1764 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር አስተወቀ። እንደ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፃ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 11 ሰዎች ውስጥ 10 ወንዶች እና አንዷ ሴትሲሆኑ  ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ናቸው። እድሜያቸው ከ18…

የታላቁን ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በመጪው ሐምሌ ወር የመጀመር እቅዷን ተግባራዊ እንደምታደርግ ኢትዮጵያ አስታወቀች

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩትና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተሳተፉበት የህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ኮሚቴ በውሃ መስኖ ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አማካኝነት የግድቡን ዝርዝር የስራ ሂደት የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተከሄደበት ይገኛል። እንደ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ በሪፖርቱ የሲቪል…

This site is protected by wp-copyrightpro.com