መዝገብ

Category: የእለት ዜና

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት የተፈፀመውን የዘር ጥቃት አወገዙ

በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሀንስበርግ መጤ በተባሉ እና የደቡብ አፍሪካ ዜግነት በሌላቸው የውጭ አገራት ዜጎች ላይ የሚፈፀመውን ጥቃት የደቡብ አፍካው ፕሬዘዳንት ሲሬ ራማፎዛ በይፋ አውግዘዋል። ፕሬዘዳንቱ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ከፀጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሰሩ እንደሆነና ዕልባት ላይ እንደሚደረስም ጨምረው አስታውቀዋል።…

ዳሰሳ ዘማለዳ ማክሰኞ ነሐሴ 28/2011

1-በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ስር ለተሰማራዉ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ላበረከተዉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አሚሶም ምስጋና አቅርቧል።ላለፉት አንድ ዓመት ኃላፊነቱን በሱማሊያ ሲወጣ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የሶማሊያ ሰላም እንዲሻሻል ከሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የሽብር ኃይሎችን ተጠራርገው እንዲወጡ  ከፍተኛ  ጥረት…

የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ካልተሻሻለ በቀጠዩ ምርጫ እንደማይሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በነሐሴ 18/2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ካልተሻሻለ በ2012 በሚካሔደው አገራዊ ምርጫ እንደማይሳተፉ ምክር ቤቱ አስታውቋል። 107 አባላት ያሉት የጋራ ምክር ቤቱ ውሳኔው 75 በመቶ የሚሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋም እንደሆነም ምክር…

ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለጉብኝት ክፍት ሊሆን ነው

ማዕከላዊ  ወንጀል ምርመራ ጳጉሜ 5/2011 የሚከበረውን ፍትሕ ቀን ምክንያት በማድረግ ከጳጉሜ 1 እስከ 5 /2011 ተከታታይ አራት ቀናት ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን የበዓሉ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ እና መድረክ ዝግጅት ኮሚቴ አስታውቋል። የኮሚቴው ሰብሳቢ ዝናቡ ቱኑ እንዳስታወቁት በቀደሙት ጊዜያት ሥፍራው በርካታ ሰብዓዊ መብት…

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያሉ ኹሉም ሼዶች በ2012 ወደ ስራ ይገባሉ

የሐዋሳ ኢንዳሰትሪያል ፓርክ አስተዳደር እና በፓርኩ የሚገኙ ድርጅቶች በቅርቡ ኹሉንም ሼዶች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት እየሰሩ መሆኑን የፓርኩ አስተዳደር ገለጸ፡ የሐዋሳ ኢንዳሰትሪያል ፓርክ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍጹም ከተማ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት የተገነቡት 52 ሼዶች ለ21 ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ የተከፋፍሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ የቅድመ ዝግጅት ስራ እንደጨረሱ ገልጸዋል፡፡ የተገነቡትን ሸዶች ከያዙት 21 ድርጅቶች ዉስጥ ብዙዎቹ አራት እና አምስት ሼዶችን የያዙ ሲሆን፡ እነዚህ ድርጅቶችም ኢንዳስተሪያል ፓርኩን በሚቀጥለው ዓመት 2012 ሙሉ በሙሉ ወደስራ ለማስገባት የሚያስችሉ ማሽነሪዎችን የመትከል ስራ ለማከናወን የሚስችላቸዉን የቅደመ-ዝግጅት ስራ እያከናወኑ እንደሆነ አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡ እንደ  ፍፁም ማብራሪያ  የተገነቡት 52 ሼዶች ሙሉ በሙሉ ወደስራ ሲገቡ አሁን በፓረኩ ዉስጥ የተፈጠረዉን 27ሽሕ የስራ ዕድል ወደ 60ሽሕ ከፍ እንደሚያደርገዉ ገልፀዋል፡፡ በቀጥታ ከሚፈጠረዉ 60ሽሕ የስራ ዕድል በተጨማሪም በዐስር ሽዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቀጥተኛ ያልሆነ የስራ ዕድል እንደሚፈጥርም ለአዲስ ማለዳ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኩ በዋናነት ታስቦ ከተገነባበት ዋነኛ ዓላማ በተለይም ኢንቨስትመንትን ከመሳብ እና ስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ የኢኮኖሚ መነቃቃትእንደፈጠረ የፓርኩ ዋና አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡ በቻይናዉ ግዙፍ ሲቪል ምሕንድስና ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን CCECC የተገነባዉ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ 2008 በጀት ዓመት ነበር ተጠናቆ የተመረቀዉ፡፡ የሐዋሳ ኢንዱስትረ ፓርክ የፕሮጀክት ማናጀር ሶንግ ዋንግ በበከሉ ኢንዳስትሪል ፓርኮቹ ዓለም አቀፍ መስፈረትን መሰረት አድርገዉ የተገነቡ እንደሆኑ ይገልፃል፡፡ CCECC ከሐዋሳ ኢንዱሰትሪ ፓርክ በተጨማሪም በመላ ኢትዮጵያ የገነባቸዉ ኢንዱሰትሪ ፓረኮች የኢትዮጵያን እንቨስትመንት የመሳብ እቅድ እና ዓለም አቀፍ ልምድን መሰረት ያደረጉ እንደሆኑ ሶንግ ገልፀዋል፡፡

ዳሰሳ ዘማለዳ ሰኞ ነሐሴ 27/2011

  ኢትዮጵያ እና እስራኤል በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ኹለቱ ወገኖች በሳይበር ደኅንነት፣ በቴሌኮምኒኬሽ እና በጠፈር ሳይንስ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። (አዲስ ማለዳ) …………………………………………….. የጀርመን ፓርላማ አባላት ከምክትል አፈ ጉባኤ ሽታየ ምናለ ጋር ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በማዘመን ዙሪያ…

80 የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የተለያዩ 17 የዓለም አገራት ዜግነት ያላቸው 80 የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በ2011 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በቁጥጥር ሥር መያዛቸውን የፌደራል ፖሊስ የፀረ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ግብረ ኃይል አስታውቋል። ከግለሰቦች ጋር አብሮ የተያዘው የዕፅ መጠን 186 ኪሎ ግራም ኮኬይን፣ 9 ኪሎ ግራም ሔሮይን…

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በዓለም አቀፉ የከንቲባዎች ጉባኤ ላይ ሊሳተፉ ነው

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በዓለም አቀፉ ከንቲባዎች ጉባኤ ላይ ሊሳተፉ ነው ዓለም አቀፉ የከንቲባዎች ጉባኤ ‹‹ሲ-40›› ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ምክትል ከንቲባ በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሀገን የሚካሔደውን ጉባኤ እንዲታደሙ ግብዣውን አቅርቧል፤ ምክትል ከንቲባውም እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በቀጣዩ ዓመት ከመስከረም 28 እስከ…

ቱርክ በተመረጡ 17 አገራት ላይ የወጪ ንግዷን በእጥፍ ለመጨመር ማቀዷን ይፋ አደረገች

ቱርክ ለዓለም ገበያ ምታቀርባቸውን ምርቶች በተመረጡ 17 አገራት ላይ በአምስት ዘርፍ የምትልካቸውን ምርቶች እጥፍ ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋለች። ከተመረጡት አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ከአፍሪካ ውስጥ ደቡብ አፍሪካን እና ኬንያን ጨምሮ ሦስት አገራት መሆናቸው ታውቋል። ቱርክ የወጪ ንግዱን በዕጥፍ ለማድረግ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ አርብ ነሐሴ 24/2011

አዲስ አበባ የሚገኘው የሮያል ዴንማርክ ኢምባሲ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት የሚያስችል ፕሮጀክት ለመጀመር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ጀምሯል።በውይይቱ የሰላም ሚንስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፋይናንስ ደኅንነት ማዕከል ተሳታፊ ሆነዋል። (አዲስ ማለዳ) ………………………………………….. የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር ዛሬ ነሐሴ…

ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው

በየዓመቱ የሚካሔደው እና ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የሚደረገው ዓመታዊው  የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተባባሪ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሔዳል። ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፎረሙ በቀጣዩ ዓመት 2012 መስከረም ላይ እንደሚካሔድ የታወቀ ሲሆን በአዲስ አበባ ስካይ ላይት…

This site is protected by wp-copyrightpro.com