መዝገብ

Author: ጌታቸው መላኩ

ከሥልጠን ጀርባ የድብቅነት ሥነ ልቦና አባዜ

አብዛኞቻችን የድብቅ ሥነ ልቦና ተጠቂዎች ነን የሚሉት ጌታቸው መላኩ፥ ከግለሰብና ቤተሰብ አልፎ በአገር ደረጃ ዋጋ እያስከፈለን ነው ሲሉ ከዘርፈ ብዙ የሕይወት ገጠመኞች በመጨለፍ ማሳያዎችን አነሳስተዋል፤ መፍትሔውንም ግልጽ ሥነ ልቦናን ማሳድግ ነው ሲሉም ምክረ ሐሳብ ሰንዝረዋል።   በትርክት ሰምተን ከፅሁፍ ሰነዶች…

ኢዜማ “አሮጌ ሐሳብን በአዲስ ልብስ” ወይንስ “የወይን ጣዕሙ መቆየቱ”

ጌታቸው መላኩ አንጋፋዎቹ ፖለቲከኞች በአዲሱ ትውልድ አቻዎቻቸው በአንድ ፓርቲ ውስጥ አብሮ በመሥራት ሒደት ሊያጋጥማቸው ስለሚችሉት ተግዳሮቶች የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲን እንደማሳያ በመጥቀስ ሐሣባቸውን አቅርበዋል።   ሰሞኑን አንድ ለውጥ ተኮር በተለይ ድርጅታዊ ለውጥ ተኮር ጉዳይ ላይ ሐሳቤን እንዳካፍ በአንድ…

ልብ ያለው ልብ ይበል!

ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሔደው የዓለም ዐቀፍ የፕሬስ ቀን አንድ በውጪ አገር ድርጅት የተዘጋጀውንና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ለውጥ ላይ የሚያተኩር አግላይ (በዝግ የተካሔደ) የጎንዮሽ መድረክን መነሻ በማድረግ ጌታቸው መላኩ ይህ ድርጊት አገራችን በሌሎች እንድንጠለፍ ዕድል መክፈቻ በር ሊሆን ከመቻሉ ባሻገር በተለይ የመንግሥትን…

ባለኹለት አፍ መንግሥት

አንድ ዓመት ያስቆጠረው የዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባሕርይ ከታዋቂው ገጣሚና ጸሐፊ ከበደ ሚካኤል “ኹለት አፍ ያለው ወፍ” ከሚለው ያመሳሰሉት ጌታቸው መላኩ፥ ንጽጽራቸውን ባነሷቸው ነጥቦች አስደግፈዋል። መንግስትም ባለኹለት አፍ ባሕሪይውን ተረድቶ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት መፍትሔዎች ማምጣት አለበት ሲሉም ይመክራሉ። የዐቢይ አሕመድ…

ከተጻፉበት ወረቀት በላይ ፋይዳ የሌላቸው የፖሊሲ ሰነዶች

ከዐሥራ አምስት ቀናት በፊት ናዝሬት/አዳማ የሚዲያና ተግባቦት ፖሊሲዎች የመጀመሪያው ረቂቅ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት ለውይይት መቅረቡ ይታወሳል። ረቂቅ ሰነዱን ያነበቡት ጌታቸው መላኩ፥ ሰነዶቹ ስለዘርፉ መሰረታዊ መረጃ ካለመስጠታቸውም በተጨማሪ አንድ የፖሊሲ ሰነድ ሊያሟላ የሚገባቸውን አንኳር ጉዳዮች አላካተቱም በማለት ይተቻሉ። የሶሻሊዝምና የኮሚኒዝም…

የኹለቱ ዶክተሮች ወግ

በኢትዮጵያ የምርጫ ስርዓት የግለሰብ አሸናፊ ሳይሆን የፓርቲ አሸናፊ ብቻ እንደሚኖር ያስታወሱት ጌታቸው መላኩ በቀጣዩ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፓርቲያቸውን በማዋሐድ ይህንን ዕድል ለማስፋት ሲሞክሩ፥ መረራ ጉዲና (ዶ/ር) ደግሞ በተቃራኒው የፌዴራል ስርዓቱ ባለበት እንዲቀጥል በመጠየቅ የማሸነፊያ ዕድላቸውን ሊያሰፉ ይሞክራሉ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com