መዝገብ

Author: ግዛቸው አበበ

የራስን ዕድል በራስ መወሰን – በወላይታና በትግራይ!

የፖለቲካ አለመረጋጋት ሰላም የነሳት ኢትዮጵያ የጥያቄዎቿን መልስ አንድም በፈፌዴራል መንግሥቱ ላይ ያኖረች ይመስላል። ይልቁንም የራስን ዕድል በራስ መወሰንን በሚመለከት የሚነሱ ጥያቄዎች በተለይ በደቡብ ወላይታ እና በትግራይ ክልል አጀንዳ ሆነው ከቀረቡ ከራርመዋል። ግዛቸው አበበም የእነዚህ ኹለት ክልል ጥያቄዎች በተመሳሳይ መንገድ እየተስተናገደ…

የልጆች ደኅንነት የወላጆች ጉዳይ ነው!

ከሰሞኑ የትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያከናውኑና የ2013 የትምህርት ዘመን ከተገቢው ጥንቃቄ ጋር እንደሚካሄድ አስታውቋል። ግዛቸው አበበም ይህን ነጥብ በማንሳት ‹አልተቸኮለም ወይ› በማለት ይጠይቃሉ። ወረርሽኙን በመስጋት የጥቂት ቀናት ኹነት የሆነው ምርጫ ተራዝሞ ዘላቂ የሆነና ተማሪዎች በየእለት በአንድ ስፋር የሚገናኙበት ትምህርት መከፈቱ…

ኮቪድ-19 – በዕውቀትና በዕውቀት ብቻ የሚዋጉት ጠላት ነው!

ኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭቱን ቀጥሎ ዘግይቶ የጎበኛትን አፍሪካም እያስጨነቀ ይገኛል። ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቋቋም በሚደረግ ሂደት ውስጥ ታድያ በየጊዜው ተለዋዋጭ አካሄዶች ቢታዩም፣ በአፍሪካ ይልቁንም በኢትዮጵያ የሚታዩ ስህተቶች ግን ዋጋ እንዳያስከፍሉ እንደሚያሰጋ ግዛቸው አበበ አንስተዋል። በተለይም ባለሥልጣናትና ሹመኞች ከሙያቸውና ከሕዝብ…

ጉዞው ከአንዱ ኮሮና ወደ ብዙ ‹ኮሮናዎች› እንዳይሆን!

ከሰሞኑ በአዲሰ አበባውና በመቀሌው ቡድን መካከል የሚታየው የዛቻ ልውውጥ እንደ ዋዛ መታየት አይገባውም የሚሉት ግዛቸው አበበ፣ ቀድሞ በሕወሓትና ሻእብያ መካከል የነበሩ ተመሳሳይ መልክ ያላቸውን የቃላት ልውውጦች አውስተዋል። በቃላት መተነኳኮሱ አዲስ ነገር ስላልሆነ ቀላል ቢመስልም፣ መዘላለፎች አሁን ወደ ጦርነት ዛቻ እያደጉ…

ማይክል ሳታን ከመሰለ መሪ ይሰውረን!

አገራት ከሌሎች አገራት ጋር ያላቸውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት በጥንቃቄና በማስተዋል፣ በብልሃትም እንዲያደርጉት ይመከራል። ይህን ነጥብ መሠረት በማድረግ ግዛቸው አበበ፣ የዛምቢያ ፕሬዘደንት ሆነው ያገለገሉትን ማይክል ሳታን አውስተዋል። እኚህ ሰው ጸረ ቻይና አቋም የነበራቸው ሲሆኑ፣ ይህም አቋማቸው ሕዝባዊ ለመሆን እንዳበቃቸው የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን…

ኮሮናና የማስኩ ገበያ!

ኮቪድ-19 የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ፣ ሰዎች ማኅበራዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ አካሄድ እንዲቀይሩ ተገደዋል። አንደኛውም አካላዊ ወይም ማኅበራዊ ፈቀቅታ ሲሆን፣ ለዚህም የሚያግዙ ሳኒታይዘር፣ የእጅ ጓንትና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች ተጠቃሽ ናቸው። ይልቁንም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክን በሚመለከት መገናኛ ብዙኀን የተለያዩ ባለሞያዎችን የተለያየ…

ኮሮናና ባለሥልጣኖቻችን!

ከመንግሥት የሚጠበቀውን መንግሥት፣ ከሕዝብ የሚጠበቀውን ከሕዝብ፣ ሁሉም የየድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሚያሳስቡት ግዛቸው አበበ፣ ባለሥልጣናት በራሳቸው ዐይን ብቻ ሳይሆን ከሕዝብ በኩል ያለውን መረዳት ይገባቸዋል ይላሉ። መንገድ ላይ የሚታዩ የሰዎች እንቅስቃሴና በየስፍራው ያልተወገዱ መጨናነቆች፣ ሰዎች ፈልገው የሚያደርጉት ሳይሆን አማራጭ በማጣታቸው እንደሆነ ሊታሰብ…

ኮሮናን ተደግፈው ፎቶ የሚነሱት…!

በአገራችንና ዓለም ዙሪያ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የጤና ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች ኮሮና ቫይረስ ያመጣውን አደገኛ ችግር ለመፋለምና የሰውን ሕይወት (የሰውን ዘርም ሊሆን ይችላል) ለመታደግ ሌት ተቀን ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ስለ እምነት (ሐይማኖት) በጥልቀት…

የደራርቱ ፍልሚያ ለሰብዓዊነት ነው!!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከታጎሉ እቅዶች መካከል የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ ይገኝበታል። ከዓመት በፊት ዝግጅት የጀመረችው አዘጋጇ ቶኪዮ፣ ውድድሩ ከነአካቴው እንዳይቀርና ዝግጅቷ ሁሉ ኪሳራ ላይ እንዳይወድቅ ከወዲሁ ሰግታለች። ይሁንና ለጊዜው ውድድሩ ለአንድ ዓመት መራዘሙ አልቀረም። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ኦሎምፒክ ኮሚቴ በዚህ…

የውጭ ግንኙነት ድሽቀት!

አባይና የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት፣ አደራድሩን ሸምግሉን እያለች የተለያዩ አገራት በሮችን የምታንኳኳው ግብጽ፣ ጥቂት የማይባሉ በሮች ተከፍተውላታል። አሜሪካም በአደራዳሪነት ሥም ገብታ ወደ ግብጽ ማድላቷና ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ስትሞክር በጉልህ ታይቷክ። ግዛቸው አበበ ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ብቻ ሳይሆን አረብ አገራት…

ኢትዮጵያ ሶርያን አትሆንም!

ኮቪድ-19 የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ፣ የተለያዩ ዘረኛ አስተያየቶች በተለያየ አጋጣሚ ሲሰሙ ነበር። ይህም በተለይ በአሜሪካ በኩል ‹የቻይና ቫይረስ› እየተባለ መጠራቱ ዘረኝነትንና ጥላቻን ያስከትላል ተብሎ በመገናኛ ብዙኀን ቃሽ መቆየቱ ይታወሳል። በተጓዳኝ በኢትዮጵያ አሜሪካውያን ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ጥቃት ደርሶባቸዋል ተብሎ በመገናኛ…

የአፓርታይድ መንፈስ በኢትዮጵያ….. ?!?!

በኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ቀጥታ ስርጭት ይተላለፍ በነበረ ስብሰባ፣ አንድ አስተያየት ሰጪ ባደረገችው ንግግር አልፎም በሐሳቧ ብዙዎች ደንግጠው ነበር። ጉዳዩም የብዙኀኑ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ግዛቸው አበበ በበኩላቸው፣ ከዚህች ሴት ሐሳብ ባልተናነሰ አልፎም በባሰ መልኩ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እንዳሉ አንስተዋል። እንደውም ከኢትዮጵያ…

ኬንያ አልተንበረከከችም!

የአገር ሉዓላዊነትና ክብር አንድም በአገር መሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ይገለጣልና፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአባይ ወንዝ ላይ እየተሠራ ስላለው የሕዳሴ ግድብ ድርድር በሚመለከት የአሜሪካ አኳኋን እንዳልተዋጠላት ኢትዮጵያ በግልጽ አሳይታ ነበር። በዚህም ላይ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ለተደረገላቸው አቀባበል…

ይድረስ ለብርቱካን ሚደቅሳ!

የኢትዮጵያ የ2012 አገራዊ ምርጫ ቀኑ ተቆርጦ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተጠበቀ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ፣ የታዩ የተለያዩ ለውጦችና መሻሻሎችም ይህን ምርጫ ፍትሐዊ ይሆናል ተብሎ እንዲጠበቅ አድርጎታል። ከዚህም ለውጥ አንደኛው ብርቱካን ሚደቅሳ የቦርዱ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸው ነው። ግዛቸው…

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ፖለቲካ!

ከሰላም ማጣት፣ ሽብርተኝነትና የአየር ንብረት ለውጥ ጎን ለጎን የዓለም አራትን ጭንቅ ውስጥ የከተተው ኮሮና ቫይረስ አሁንም እየተስፋፋ ይገኛል። አገራትም በየራሳቸው መንገድ ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግና ሕዝባቸውን ለመጠበቅ የየበኩላቸውን ያሉትን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ግዛቸው አበበ ታድያ የኢትዮጵያን ሁኑታ አንስተው የአየር መንገዱን ‹በረራ አላቆምም›…

ኦሮምያ እንደ ትግራይ- ጅማም እንደ ዓድዋ??!!

በኢትዮጵያ የተካሄዱ አገራዊ ምርጫዎች በየጊዜው የየራሳቸውን አይረሴ ኩነቶች አስተናግደው አሳልፈዋል። ግዛቸው አበበ እነዚህን ይልቁንም የ1997 ምርጫና የ2002 ምርጫን በማንሳት፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ሁኔታ ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ በምርጫዎች ዋዜማ፣ በምርጫ ወቅትና በምርጫ ማግስት እንደ አገር ካስተናገደችው ግርግር ውስጥ በትግራይ ክልል የነበረውን ክስተት…

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከማላዊው አቻው ውድቀት ይማር!

ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ጫናዎች ስር ነው። ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ እንደሆነ ቢነገርና ምርጫውም ነጻና ፍትሐዊ ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አካሄዱ ግን ወደዛ እንዳልሆነና እንደማይመስል ያብራራሉ። ጠቅላይ ሚስትሩ በተወካዮች ምክር ቤት ያደረጉትን ንግግርና የሰጡትንም ምላሽ፣ ይልቁንም ከምርጫ ጋር የሚገናኙ ነጥቦች አወዛጋቢ ከመሆናቸው…

የአፍሪካ ኅብረት ለፍልስጥኤም ምን ይፈይድ ይሆን?

አንድም የፍልስጥኤም ተወካይ ባልተጋበዘበት ነበር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “..የእስራኤልንና የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሕይወት የማሻሻል ርዕይ የሰነቀ የሰላምና ብልጽግና ርዕይ ነው” ያሉትን እቅድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ያደረጉት። ይህንንም ተከትሎ ከተባበሩት መንግሥታትም የፍልስጥኤምን አገረ-መንግሥትነትን የተቀበሉ በርከት ሲሉ አሜሪካንና እስራኤልን ጨምሮ ጥቂቶች…

ያልተቀረፈው አገር ‹ማጥፊያ› ስትራቴጂ!

በኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚታዩ ችግሮች መነሻዎች የፖለቲካ ሹመኞች ብቻ ሳይሆን ምሁራንንም ይመለከታል የሚሉት ግዛቸው አበበ፣ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ያነሳሉ። በትክክል ሳይማሩ ወረቀትንና ውጤትን በገንዘብ የሚገዙ ሰዎች በጊዜ ሊፈታ የሚገባውን ችግር ባለመፍታታቸው ዛሬ ላይ ደርሰናል ሲሉም ይሞግታሉ። ይህ አገርን የሚያጠፋ ልብ…

ምርጫውን ከወዲሁ የመቆጣጠር ሩጫዎች!

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ጊዜያዊ ሰሌዳ መሠረት፣ ነሐሴ ወር የ2012 አገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት ወር ነው ተብሎ ይጠበቃል። የምርጫ ቅስቀሳዎችም የሰሌዳውን መጽደቅ ተከትሎ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንደሚከናወን ይጠበቃል። ምርጫው ፍትሐዊ እንዲሆን የሚጠበቅ ሆኖ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ግን አስቀድሞ የመወሰን ሥራ እየተሠራ ነው…

ዳግም ምጽአት ‘ሐለዋ ወያነ-ወ-ፈዳያን’!

ሕወሓት በመቀሌ ከተማ ታኅሳስ 18 እና 19 እንዲሁም ታኅሳስ 25 እና 26/ 2012 ያደረጋቸውን አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ ተነሱ የተባሉ ጉዳዮችን መሠረት አድርገው የተነሱት ግዛቸው አበበ፣ ከስብሰባው ቀድሞ በትግራይ ተወላጆች መካከል የነበረውን ስሜት ቃኝተዋል። እንዲሁም ከስብሰባው በኋላ በቀረበው የሕወሓት የአቋም መግለጫና…

የ‹ዲ ፋክቶ› መንግሥት 30ኛ ዓመት!

የ›ዲ ፋክቶ›ን ጽንሰ ሐሳብና ምንነት የሚጠቁሙት ግዛቸው አበበ፥ ልብ አልተባለም እንጂ ቀድሞም በኢትዮጵያ ይልቁንም በትግራይ ክልልና በሕወሓት አገዛዝ የ‹ዲ ፋክቶ› መንግሥት ባህርያት ይታዩ ነበር ይላሉ። እንደውም ሠላሳ ዓመት ሞልቶታል ሲሉ ይጠቅሳሉ። አሁን ላይ ስለ መገንጠልና መለየት እንዲሁም ስለ ‹ዲ ፋክቶ…

በፖለቲካ አመለካከት መለየት ሐጢአት አይደለም!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር እና የኦዲፒ ምክትል ሊቀመንበር ለማ መገርሳ በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች የሚደረገውን ውህደት እንደማይቀበሉ ከተናገሩ በኋላ፣ ከተለያየ አቅጣጫ የተለያዩ ሐሳቦች ሲናፈሱ ነበር። የሐሳብ ልዩነታቸውንም ከሐሳብ ልዩነት ባለፈ የተለያየ ግብረ መልስ አስተናግዷል። ግዛቸው አበበ ይህን ነጥብ በማንሳት ለማ መገርሳ አስቀድሞ…

የአዲስ አበባና የመቀሌ መንግሥቶቻችን ፉክክር!

አዲስ አበባ እንዲሁም መቀሌ ላይ የተከናወኑ ስብሰባዎች በየበኩላቸው ኢትዮጵያን ለማዳን ቆመና ሲሉ ተሰምተዋል፤ የአዲስ አበባው ብልጽግና ፓርቲን በማጽደቅ፣ የመቀሌው በአንጻሩ በመቆምና በመተቸት። ይህን ክስተት መነሻ በማድረግ ሐሳባቸውን ያጋሩት ግዛቸው አበበ፤ በኹለቱ ስብሰባዎች መካከል ስላሉ መመሳሰሎችና ልዩነቶች የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል። እንዲሁም…

ከኢሕአዴግ ወደ ኢብፓ/ብፓ ጉዞ …!!

የኢሕአዴግን ምሥረታ ቀደም ካለው ከሕወሓት አነሳስና ቀዳሚ ዓላማ በመጀመር የሚያወሱት ግዛቸው አበበ.፤ አሁንም ላይ በግንባሩ የሚገኙት ፓርቲዎች አጋር ሲሏቸው የቆዩትን ጨምረው ስለሚመሠርቱት ‹ብልጽግና ፓርቲ› አንስተዋል። ይህ በኢሕአዴግ ጀምሮ ወደ ብልጽግና ፓርቲ እየተደረገ ባለው ጉዞም፣ የሕወሓትን ሁኔታ ዳስሰዋል። አሁንም ኢሕአዴግ አስቀድሞም…

ስርዓት አልበኝነቱን ማቆሚያ የት ይሆን!?

ለሰሞኑን ግጭት መነሻው ለውጥ ከመምጣቱ በፊት የነበረው ኢሕአዴግ በሕዝቦች መካከል አንብሮት የነበረው የከፋፍለህ ግዛ ውጤት ነው የሚሉት ግዛቸው አበበ፥ ወጣቶቹ ወደ እርስበርስ መናቆር ከማምራታቸው በተጨማሪ ምንም ዓይነት የጠራ ዓላማና ስትራቴጂ፣ ተጋፋጭነትና ቁርጠኝነት ሳይኖራቸው ስለሚንቀሳቀሱ ለሕዝቦቻቸው ሰቆቃዎችን እያሸከሙ መጥተዋል ይላሉ። ግዛቸው…

መቀመቅ ቁፋሮ በማን እና ለማን ነው?

ግዛቸው አበበ ሰሞኑን መተማ-ሱዳን መንገድ መዘጋቱ እና በአካባቢው (በጭልጋ) ለቀናት ጦርነት አከል ግጭት መኖሩን በተለያዩ መገናኛ ብዙኀን መዘገቡን በማስታወስ ከሰሊጥ ምርትና ወጪ ንግድ እንዲሁም ከቅማምት ማኅበረሰብ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ግጭት አንድምታ በመጣጥፋቸው አመላክተዋል። የፌደራል መንግሥቱ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ መግባት ይገባዋልም…

የዐቢይ አካሔድ በወላይታ፡- “በመጀመሪያ ‘በዱርሳ’ ከዚያም ‘በእርሳስ’ ነው”

የወላይታ ሕዝብን የክልልነት ጥያቄ ለማፈን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሔዱበት አካሔድና የኋላ ኋላ የወሰዱት እርምጃዎች፥ ክልሎችን በኀይል ለመቆጣጠር፣ መዋቅራቸውን ለመበጣጠስና ህልውናቸውን ሽባ ለማድረግ ነው የተጠቀሙበት ሲሉ ግዛቸው አበበ መከራከሪያቸውን አቅርበዋል።   ከአማርኛ ጭፈራዎች አንዱ እስክስታ እንደሚባለው የወላይታ ባሕላዊ ጭፈራ…

ወታደራዊ አስተዳደር በደቡብ፣ ‘የእናት አገር ጥሪ’ በትግራይ!

የፌደራል መንግሥቱ ሐምሌ 11 ከሲዳማ ክልልነት ጋር በተያያዘ የተከሰተውን ኹከት ሌሎች የክልልነት ጥያቄዎችን ጸጥ ለማሰኘት ተጠቅሞበታል፤ የትግራይ ክልል መንግሥት በበኩሉ ባለፈው ሳምንት የንግዱ ማኅበረሰብ አስተባበረው የተባለውን ‘ቴሌቶን’ሕወሓት ሕዝባዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ ተጠቅሞበታል በማለት ግዛቸው አበበ ያትታሉ። ለውጥ መጣ ከተባለ በኋላ፣ ጠቅላይ…

መብረቁ ብልጭ ሲል ደማሚቱን ማፈንዳት! የጄኔራል ሰዓረ አሟሟት በቅጡ ይፈተሽ!

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15 በባሕር ዳርና በአዲስ አበባ በሰዓታት ልዩነት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን(ዶ/ር)‘ን ጨምሮ ሌሎች ኹለት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የጦር ኀይሎች ኤታ ማዥር ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሌላ አንድ ጡረተኛ ከፍተኛ የጦር መኮንን ግድያዎች ምክንያት በመላው አገሪቱን ሐዘንና ድንጋጤ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com