መዝገብ

Author: ስንታየሁ አባተ

የዳኞች ምልመላ ከፍርድ አሰጣጥ ጥራትና ከመዝገብ ክምችት አንጻር

እንዲህም ያሉ የሕግ ባለሙያዎች?! ሰዓቱ የምሳ፣ ቦታው ደግሞ ምዕራብ ወለጋ ነቀምት አካባቢ ነው። መንገድ ዳር ካለ አንድ ሥጋ ቤት በረንዳ ላይ አረፍ ብለው ምሳቸውን የሚመገቡ ሰዎች አሉ። ከተማዋ ደግሞ የመንገድ ጥበት ካለባቸውና በጋውን በአቧራ፥ ክረምቱን ከጭቃ እምብዛም ከማይርቁት ኢትዮጵያዊያን ከተሞች…

የለውጡ እርምጃ ከፍፁም እምነት ወደ ጥርጣሬ ጎዳና

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከመጋቢት እስከ መጋቢት በሚል ርዕስ ባለፈው አንድ ዓመታት የተመዘገበውን ለውጥ የመወያያ ርዕስ አድርጎታል። ስንታየሁ አባተ የተለያዩ ምሁራን ስለ ለውጡ የተናገሩትን መሠረት በማድረግ የለውጡ እርምጃ አነሳሱ ላይ ከአነገበው ተስፋ በብዙ ምክንያቶች እየተነጠለ የጥርጣሬ ጎዳና ፊቱ ተጋርጦበታል በማለት፥…

የመገናኛ ብዙኀን የኅዳሴ ግድቡን ረስተውታል በሚል ተወቀሱ

የመገናኛ ብዙኀን አውታሮች የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ግንባታን በተባራሪ ዘገባ ከመሸፈን ባለፈ የብሔራዊ መግባቢያ አጀንዳ ማድረጉን ረስተውታል የሚል ወቀሳ ቀረበባቸው። የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽሕፈት የተጣራ መረጃን ይዞ ወደ መገናኛ ብዙኃን ለመቅረብ ወራትን ስለፈጀሁ የፕሮጀክቱ የዘገባ ሽፋን እንዲቀንስ አንድ…

ዐቢይ ላይ የተንጠለጠለው የአፍሪካ ቀንድ ጉዞ

የአፍሪካ ቀንድ መልክ የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በዓለም የተወሳሰቡና የግጭት አካባቢዎች ከሚባሉት አንዱ ስለመሆኑ የሚያስታውሰው እና ኤስኤስአርሲ በተሰኘ የበይነ መረብ ገጽ ላይ የወጣው ʻCrisis in the Horn of Africaʼ የተሰኘ ጽሑፍ የአፍሪካ ቀንድ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን እና…

ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንትና የቦርድ አባል ውስጥ ግማሾቹ ሴቶች እንዲሆኑ ታዘዘ

በዩኒቨርሲቲ የፕሬዘዳንትነትና የቦርድ አባልነት ስብጥር ውስጥ ግማሾቹ ሴቶች እንዲሆኑ ለዩኒቨርሲቲዎች መመሪያ መስጠቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ። ሚንስትሯ ሒሩት ወልደማሪያም (ፕሮፌሰር) ለአዲስ ማለዳ ልዩ እትም መጽሔት እንግዳ ሆነው በቀረቡበት ቃለ ምልልስ እንዳሉት ለሚንስቴሩ ተጠሪ በሆኑት 45 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኘው…

ዕጣ የወጣባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶች የጋዜጣ ሕትመት ተቋረጠ

ባለፈው ረቡዕ የካቲት 27/2011 እጣ የወጣባቸው ከ52 ሺሕ የሚጠጉ የ20/80 እና 40/60 መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር በጋዜጣ እንዳይታተም ታገደ። ለወትሮው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲተላለፉ የእድለኞችን ዝርዝር ይዞ የሚጣውና በአዲስ አበባ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ስር የሚታተመው አዲሰ ልሳን ጋዜጣ እንደሆነ ይታወቃል። ጋዜጣው…

በሐረር መሬቱ የእኛ ነው ያሉ ቡድኖች ሕጋዊ ቤቶችን ማፍረሳቸው አስቆጣ

• የመንጋ አካሔድ ተስተውሏል ያለው ክልሉ ቤት ፈረሳው የእኔ ፍላጎት አይደለም ብሏል በሐረር ከተማ ቀበሌ 16 ቤቶቹ የተሰሩት በእኛ መሬት ላይ ነው ያሉ ሕገ ወጥ ቡድኖች መጤ ናቸው ያሏቸውን ነዋሪዎች ሕጋዊ ቤቶችንም ጭምር ማፍረሳቸውን ተከትሎ አለመረጋጋት መከሰቱ ተገለጸ። የሐረሪ ክልል…

የትግራይ መንግሥት በአማራ ላይ አፈሙዝ የማዞርበት ምክንያት የለኝም አለ

የትግራይ ሕዝብና መንግሥት በወንድሙ የአማራ ሕዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞርበትና ጦርነት የሚገጥምበት ምንም ምክንያት እንደሌለው የክልሉ የሕዝብ ግንኙነትና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ። የአማራ ክልል ምክር ቤት በአማራና በትግራይ መካከል ጦርነት ለመክፈት የሚሰሩ ወገኖችን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። በአማራና በትግራይ ሕዝቦች መካከል ጦርነትን…

˝የአማራን ነፃነት ለማስከበር ፍቱን መፍትሔው መደራጀትና መወያየት ነው˝

˝የአማራን ሕዝብ መብት፣ ጥቅም፣ ክብርና ነፃነትን ለማስከበር ፍቱን መፍትሔው መደራጀትና መወያየት ነው˝ ሲሉ አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) አስታወቁ። የአማራን ሕዝብ መብት፣ ጥቅም፣ ክብርና ነፃነትን ለማስከበር ፍቱን መፍትሔው መደራጀትና መወያየት መሆኑን የክልሉ መንግሥት እንደሚያምን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ…

አድዋ ትናንትና- ዛሬ

123ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ድሉ ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ምን ያስተምራል? ከታሪክ በመማር በኩል ምን ጎደለን? በቀጣይስ ምን ማድረግ አለብን? አፍሪካዊያን የአድዋን ድል ‹የእኛ ታሪክ ነው› በሚሉበት ዘመን ኢትዮጵያዊያን እንዴት እየተማርንበትና የአንድነታችን ማጠንከሪያ እያደረግነው ነው? በተጨማሪም ድሉን የታሪካችን ምርምር አንድ…

የኤርትራው ልዑክ እና የሦስቱ ከተሞች ምርጫ

ከሰሞኑ 55 አባላትን የያዘው የኤርትራው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት (‘ፐብሊክ ዲፕሎማሲ’) ልዑክ የኢትዮጵያንና ኤርትራን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግና ሕዝባዊ ሥር ለማስያዝ በሚል በኢትዮጵያ አራት ከተሞች መዘዋወሩ ይታወሳል። ይፋዊ ጉብኝቱንና ባሕላዊ ትርዒት ማቅረቡን የካቲት 8/2011 ከባሕር ዳር የጀመረው ልዑኩ በአዳማና ሐዋሳ…

77 ሺሕ ተፈናቃዮች ቢኖሩኝም ማዕከላዊ መንግሥቱ ዜጎቼ አላላቸውም ሲል የትግራይ ክልል ወቀሰ

• ኮሚሽኑ እርዳታን በደብዳቤ ጠይቆ የተከለከለ ክልል የለም ብሏል “በብሔር ትግራዋይ በመሆናቸው ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ 77 ሺሕ የትግራይ ተወላጆች አሰቸኳይ ድጋፍ ቢፈልጉም፣ ማዕከላዊ መንግሥቱ ዜጎቼ ብሎ አላያቸውም፤ መልሶ ለማቋቋምም እየሠራ አይደለም›› ሲል የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወቀሰ፡፡ የክልሉ መንግሥት…

ምርጫ ቦርድ መጀመሪያ አመኔታ የሚያስገኙልኝን ሥራዎች አስቀድማለሁ አለ

የሲዳማ ክልል የመሆንን ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሔድም ይሁን በመጪው ምርጫ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ መጀመሪያ አመኔታን የሚያስገኙለትን ቁልፍ ሥራዎች መሥራት እንዳለበት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። የሲዳማ ዞን ሕዝብ የክልል እንሁን ጥያቄ በክልሉ ምክር ቤት ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ የሕዝበ ውሳኔው ቀን ቶሎ…

850 አውቶቡሶችን ለሚያስተናግደው የየካ ዴፖ ተቋራጮች እየተመረጡ ነው

ከ850 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ እንዲያስችል በ10 ሄክታር መሬት ላይ ለሚገነባው የየካ አውቶቡስ ዴፖ ከ10 በላይ ተቋራጮች በቅድመ ጨረታ መረጣ ላይ መሆናቸውን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ገለፀ። የግንባታ ሥራው ኹለት ዓመት እንደሚፈጅ የታቀደውን ዴፖ ግንባታ ለማስጀመር…

‘ከይጀመራል ማለፍ ያልቻለው’ የፈጣን አውቶብስ መስመር ግንባታ

የተጨበጠ ነገር ሳይያዝ ፕሮጀክቶችን እጀምራለሁ ማለትን ተለማምዳለች በሚል የምትታማው አዲስ አበባ ከዘጠኝ ዓመት በፊት (2002) እጀምረዋለሁ ያለችውን የከተማ ፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ እስካሁን አልጀመረችም። ይኸው ፕሮጀክት የውሃ ሽታ ይሁን እንጂ የከተማ አስተዳደሩ ከዓመታት በፊት ከፈረንሳይ ልማት ድርጅት (‘ኤኤፍዲ’) የተበደረው የ50…

‘ቤት የራባቸው’ የአዲስ አበባ ቦታዎች

በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 9 ለሪል እስቴት ግንባታ የተሰጠና እስካሁን ቤት ሳይገነባበት ያለ 92 ሺ 721 ካሬ ሜትር ቦታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎቿ ቤት አልባ የሆኑባት አዲስ አበባ “ጣሪያ የነካውን የቤት ፍላጎት ያቃልሉልኛል” በሚል የቤት አልሚ ኩባንያዎች (‘ሪል ኢስቴት’) ልማትን ከተዋወቀች ዐሥርት…

በማኅበራት ቤት ለሚገነቡ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የቅድሚያ ቁጠባ ዋጋ ሊቀነስላቸው ነው

• 960 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ከሪል ኢስቴት አልሚዎች ተነጥቆ ለኅብረት ሥራ ቤት ግንባታ ሊተላለፍ ተወስኗል የአዲስ አበባ አስተዳደር የቤት ልማት ትኩረት ከኮንዶሚኒየም ወደ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ቤት ግንባታ መዛወሩን ተከትሎ በጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው የነበሩ ነዋሪዎች ዝቅተኛውን ቁጠባ ብቻ…

የጎዳና ተዳዳሪዎችን “እያፈሱ” ማቋቋም

የጎዳና ሕይወትን ሕይወቴ ብለው የሚኖሩ ዜጎችን ማየት የተለመደ የዕለት ትዕይንት በሆነባት አዲስ አበባ፥ የከተማ መስተዳድሩ መልሼ አቋቁማለሁ በማለት ሥራውን በይፋ ያስተዋወቀው በቅርቡ ነው። ይህንኑ ተከትሎ በአዲስ አበባ ያሉትን የጎዳና ተዳዳሪዎች ኑሮ ምን እንደሚመስል፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን መልሶ ለማቋቋም ከዚህ ቀደም የተሠሩ…

ባንኮች በማኅበራት ለቤት ገንቢ አዲስ አበቤዎች እንዲያበድሩ ሊጠየቁ ነው

በጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ከ960 ሺሕ በላይ ተመዝጋቢዎች ቢኖሩም ግንባታውን በፍላጎቱ ልክ ማከናወን የተሳነው የአዲስ አበባ አስተዳደር ተመዝጋቢዎቹ በቤት ሥራ ማኅበራት እየተደራጁ ቤት እንዲገነቡና ባንኮችም የረጅም ዓመት የገንዘብ ብድር እንዲፈቅዱ የማግባባት ሥራ ሊከውን መሆኑ ተሰማ። አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ እንደሰማችው በቤት…

የተቋረጠው 30ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ ሊጀመር ነው

በነሐሴ 2010 ተቋርጦ የነበረው 30ኛው ዙር የአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ ጨረታን ለማስጀመር ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገለጸ። የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ንጉስ ተሾመ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት አሁን ላይ ከመንፈቅ በላይ ተቋርጦ የቆየውን የከተማ መሬት ሊዝ ጨረታ…

ኦነግ ሠራዊቱን በ20 ቀናት ካምፕ ለማስገባት ተስማማ

በኦነግና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት መካከል የነበረው ቅራኔ በእርቅ ተፈቷል መባሉን ተከትሎ ኦነግ ሠራዊቱን በ20 ቀናት ወደ ካምፕ እንዲያስገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። ወታደሮቹ ወደካፕ ሲገቡ የጀግና አቀባል እንዲደረግላቸው የሚል ውሳኔ የተላላፈም ሲሆን፣ በመንግሥት በኩል ወታደሮቹ ቶሎ ወደ ካምፕ እንዲገቡ ጉጉት…

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ቀውስ

በኢትዮጵያ ባሉ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ግጭቶችን መስማት አዲስ ነገር አይደለም። የግጭቶቹ መንስዔዎች ምንም ሆኑ ምን የብሔር ገጽታ እንደሚሰጣቸውም ይነገራል። ይህንን ጉዳይ መነሻ ያደረገው ስንታየሁ አባተ፣ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ላይ ተጨማሪ ሕመም ስለሆነው እና የትምህርት ሒደትን እስከማስተጓጎል የደረሰውን የዩንቨርስቲዎች ቀውስ…

አምነስቲ የሲቪል ማኅበረሰብ ረቂቅ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ጠየቀ

አምነስቲ ኢንተርናሽል አዲሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ረቂቅ አዋጅ በምዝገባ ሒደትና እንዲሁም ጣልቃ ገብነትን በማስፋት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ማኅበራትን እንቅስቃሴን ያውካሉ ባላቸው አንቀፆች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጠየቀ። አምነስቲ ለምክር ቤቱ አባላት ጥር 16 በበይነ መረብ ላይ በጻፈው…

በድሬዳዋ ትናንት ባገረሸው ግጭት ነዋሪዎች ስጋት ውስጥ ገብተዋል

በድሬዳዋ ትናንት አርብ፣ ጥር 17 ረፋድ ላይ ባገረሸውና ፖለቲካዊ መልክ በያዘው ግጭት በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቀሰሴዎች ከመገደባቸው ባሻገር ነዋሪዎቹ በስጋት ከቤት መውጣት እንዳልቻሉ ተገለጸ። አንድ ሕጻን ሲገደል አራት ሰዎች ተጎድተዋ ተብሏል። አዲስ ማለዳ በከተማዋ ከሚኖሩ ምንጮቿ እንደተረዳችው ሰኞ፣ ጥር 13 የነበረው…

ሥሙ የከበደው የአፍሪካ ኅብረት

አዲስ አበባ አውጥታ ልትተፋቸው የማትችላቸውን የጎዳና አዳሪዎች መንገድ ላይ እንዳይታዩባት ከምትሸሽግባቸው ጊዜያት አንዱ የአፍሪክ ኅብረት የመሪዎቸ ጉባኤ ነው። ይህ ተግባሯ በነዋሪው ዘንድ ብዙ ትችት ቢያሰነዝርባትም የአዲስ አበባ አስተዳደር ግን ‹‹ገጽታዬ ይበላሽብኛል›› በሚል የኅብረቱ አባል አገራት መሪዎቸ ከቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን…

የኹለቱ ርዕሰ መስተዳድሮች መግለጫ፤ “በሕዝብ መሳለቅ?“

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራና ትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ሰላማዊ ፉክክር የሚስተናገድበትን እግር ኳስ ሳይቀር እስከ መረበሽ መድረሱ ይታወሳል። በአማራ ክልል ያለ የእግር ኳስ ቡድን ወደ ትግራይ አቅንቶ ለመጫወት እንዲሁም በተቃራኒው የትግራዩ ወደ አማራ ለመምጣት እስከ መፍራት ተደርሶ መደበኛ መርሐ…

ተማሪዎቹ ባሕር ዳርን ለቀው እንዲወጡ ክልሉ አሳሰበ

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ባሕር ዳር ከተማ በመሄድ የተጠለሉ ከኹለት ሺህ 500 በላይ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የክልሉ መንግሥት ማሳሰቢያ ሰጠ። ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው እስኪረጋጋ ድርስ ለአንድ ወር ያህል በከተማው ሕዝብ ጭምር እተየደገፉ በመጠለያ መቆየታቸውን…

በአዲስ አበባ 20 ትምህርት ቤቶች በኦሮምኛ ቋንቋ እያስተማሩ ነው

በአዲስ አበባ 20 ትምህርት ቤቶች ከቅድመ መደበኛ እስከ 9ኛ ክፍል የሚማሩ ከ12 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን በኦሮምኛ ቋንቋ እያስተማሩ እንደሚገኙ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ድርጅት እስከ 25 ሺሕ ብር ወርሃዊ ደሞዝ የሚከፈላቸው መምህራን መኖር ቅሬታን አስነስቷል። በአዲስ አበባ…

በአዲስ አበባ 78 በመቶ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ሳያሟሉ እያስተማሩ ነው

በአዲስ አበባ ከሚገኙ አንድ ሺሕ 407 ትምህርት ቤቶች 78 በመቶዎቹ የሚጠበቅባቸውን ደረጃ ሳያሟሉ እያስተማሩ እንደሚገኙ የከተማዋ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ ገለጸ። አዲስ ማለዳ ከኤጀንሲው ያገኘችው መረጃ እንደሚያሳየው በከተማዋ በግል፣ በመንግሥትና በሕዝብ የሚተዳደሩት የቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ እና ኹለተኛ ደረጃ…

አዲስ አበባን እየፈተኑ ያሉ ወንጀሎች

ቦታው ፒያሳ ሠዓሊ ግብረክርስቶስ ሰለሞን በላቸው የጥበባት ሱቅ አጠገብ ነው። አንዲት ትነሽ በላሜራ የተሰራችና ቢጫ በጥቁር የተቀባች ክፍል ትታያለች። ወደ ውስጥ ሲገቡም ክፍሏ ኹለት በኹለት ካሬ እንኳን እንደማትሞላ ይረዳሉ። በአንጻሩ ጠባብ የሚለው ቃል የማይገልጻት ክፍል አንድ ወንበርና አሮጌ ጠረጴዛ እንድትይዝ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com